ҽ

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና የደህንነት ኮሚሽነሮች በአህጉሪቱ እየተከሰቱ ባሉ ግጭቶች ላይ ያላቸውን አቋም ሲያብራሩ በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና የደህንነት ኮሚሽነሮች በአህጉሪቱ እየተከሰቱ ባሉ ግጭቶች ላይ ያላቸውን አቋም ሲያብራሩ   (AFP or licensors)

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን ጋር ባደረጉት የመልዓከ እግዚያብሄር ጸሎት ላይ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፥ በግጭት ውስጥ ለሚገኙ ሃገራት በተለይም ሱዳን ውስጥ እየተከሰተ ላለው አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ጸሎት ማድረጋቸው ተነግሯል ።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካ መሪዎች በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በማውገዝ፥ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ መሪዎቹ ጠይቀዋል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የምድር፣ የአየር ድብደባ እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ተጠናክረው በመቀጠላቸው ግጭቱ እየተባባሰ መምጣቱን ያመላክታል ተብሏል።

በኢትዮጵያ በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ሁኔታው እጅግ አስደንጋጭ እና ጭካኔ የተሞላበት ጥፋት መሆኑን በመግለጽ ግጭቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰፊውን የሃገሪቱን ክልል እያማከለ መምጣቱን አስጠንቅቀዋል።

የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከተጀመረ ወደ ሶስተኛ ዓመቱ እየተቃረበ ሲሆን፥ በነዚህም ጊዜያት ከፍተኛ የሆነ ረሃብን፣ መጠነ ሰፊ የህዝብ መፈናቀልን እና ሥር የሰደደ የጸጥታ እጦትን ማስከተሉ ተገልጿል።

ከዚህም በላይ ከጠቅላላው ሕዝብ ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆነው ማለትም ወደ 30.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአሁኑ ወቅት የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች የሰብአዊ ድጋፍ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በሃገሪቷ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግጭት ኢኮኖሚያዊ ውድቀትን ያስከተለ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት የምግብ፣ የነዳጅ እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ እየናረ በመምጣቱ ተራው ዜጋ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደሚገኝም መረጃዎች ያመላክታሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚከናወኑ የእርዳታ ስራዎች የሚውል 4.2 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
 

17 Feb 2025, 14:29