ҽ

2019.05.17 Conferenza robotica casina Pio IV

ቫቲካን በግብር ማሻሻያ ሐሳቦች ላይ ዓለም አቀፍ ውይይት እያስተናገድች ትገኛለች

የኖቤል ተሸላሚው ኢኮኖሚስት አቶ ጆሴፍ ስቲግሊትዝ እና የኤችአይቪ/ኤድስ በሽታን ለመዋጋት የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት የጋራ ፕሮግራም (UNAIDS) ዋና ጸኃፊ ወ/ሮ ዊኒ ቢያኒማ በጳጳሳዊ የማህበራዊ ሳይንስ አካዳሚ አስተናጋጅነት ግብር ማሻሻያ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ውይይት እየተደርገ መሆኑን ከቫቲካን ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

 የተባበሩት መንግስታት የጋራ ፕሮግራም በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ የተፋጠነ፣ ሁሉን አቀፍ እና የተቀናጀ ዓለም አቀፍ እርምጃ በመውሰድ ወረርሽኙን ለመግታት የሚሰራ ድርጅት ነው።

በደርዘን የሚቆጠሩ የሃገር አቀፍ መንግስታት እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ባለስልጣናት በቫቲካን 'የታክስ ፍትህ እና አንድነት' ላይ በከፍተኛ ደረጃ የሚደረግ ውይይት ሐሙስ እለት የካቲት 06/2017 ዓ.ም ተሰብስበው ነበር።

በጳጳሳዊ የማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ (PASS) የተዘጋጀው ጉባኤ የዛሬው ዓለም አቀፍ የግብር ሥርዓት ዓለም አቀፋዊ አለመመጣጠንን የሚያቀጣጥልበትን መንገዶች ዳሷል።

በኢኮኖሚ ማሻሻያ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ 'መምራት' ሚና

የግብር ማሻሻያ “ወሳኝ ነው” ሲሉ የጳጳሳዊ የማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሲስተር ሄለን አልፎርድ ለቫቲካን ዜና ተናግረዋል።

አሁን ያለው የአለም አቀፍ የግብር ስርዓት ከመቶ አመት በላይ ያስቆጠረ ነው ሲሉ አፅኖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ከዛሬው ልዕለ-ዓለም አቀፋዊ ዓለም ጋር "በእርግጥ መቋቋም አልቻለም" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ አለምአቀፋዊ ኮርፖሬሽኖች እና እጅግ ባለጸጋ ግለሰቦች በጣም ዝቅተኛ የግብር ክፍያ እንዲከፍሉ ያስችላቸዋል፣ ይህ ደግሞ መንግስታትን ወሳኝ ግብአቶችን ያሳጣቸዋል ብለዋል።

ሲስተር አልፎርድ ችግሩን በመዋጋት ረገድ ቤተክርስቲያን የምትጫወተውን ሚና አበክሮ ገልጿል። በደርዘን የሚቆጠሩ የመንግስት እና የአለም አቀፍ ባለስልጣናት በቫቲካን ለከፍተኛ ደረጃ ውይይት ተሰብስበው ነበር ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ምክንያቱም ቤተክርስቲያን እና በተለይም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዛሬው ዓለም የሚጫወቱትን “ወሳኙን የመመሪያ ሚና” ስለሚገነዘቡ ነው ብለዋል።

መሪዎቹ ከዓለም 1.4 ቢሊዮን ካቶሊኮች ጋር ብቻ ሳይሆን የመናገር ችሎታቸውን ይገነዘባሉ ያሉት ሲስተር አልፎርድ፣ “ነገር ግን ከዚህም ባሻገር”፣ ጳጳሱ ከቤተክርስቲያን ውጭ ባሉ በብዙዎች ዘንድ እንደ የሞራል ባለሥልጣን ተደርገው እውቅና ተሰጥቶዋቸዋል ብለዋል።

ከዚህም በላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በሌሎች የባለብዙ ወገን ድርጅቶች ላይ ያሉ ችግሮች ማለትም እንደ የጳጳሳዊ የማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ ያሉ ቦታዎች ላይ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል ያሉት ሲስተር አልፎርድ የመንግስት ባለስልጣናት እና የአለም መሪዎች "ስለ ሌላ ቦታ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆኑ ሀሳቦች" እንዲወያዩ እድል ይሰጣል ብለዋል።

የግብር ማሻሻያ እና ኢዮቤልዩ

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የኖቤል ሽልማት አሸናፊው ኢኮኖሚስት እና የጳጳሳዊ የማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ ጸኃፊ የሆኑት አቶ ጆሴፍ ስቲግሊዝ ይገኙበታል።

የግብር ማሻሻያ እና ኢዩቤሊዩ

ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቤተክርስቲያኒቱ በግብር ማሻሻያ ጉዳይ ላይ ላሳየችው “የሞራል አመራር” አመስግነዋል፣ ውይይቱ የመጣው እ.አ.አ በ2025 ኢዮቤልዩ ዓመት ለ“ፍትህና እኩልነት” በተዘጋጀው አውድ ውስጥ መሆኑን ጠቁመዋል። "የግብር ፍትህ እንፈልጋለን" ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

ቢሊየነሮች እና ሀብታም ኮርፖሬሽኖች ተገቢውን የግብር ድርሻቸውን የሚከፍሉ ከሆነ ብቻ ነው አቶ ስቲግሊትዝ እንዳሉት ከሆነ "ለበለጠ እኩልነት የሚደረግ እንቅስቃሴ" እና "በስርዓታችን ላይ እምነት ወደነበረበት መመለስ" ሊኖር የሚችለው ሲሉ ተናግረዋል።

ከኤችአይቪ እና ኤድስ ጋር የሚደረግ ትግል

ከጉባኤው ጎን ለጎን የተባበሩት መንግስታት የኤችአይቪ/ኤድስ የጋራ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዊኒ ቢያኒማ ቫቲካን ኒውስ ጋር ለማነጋገር እድል አግኝተው ነበር።

ዊን ባይኒማ ድርጅቱ በሽታውን እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም ለማጥፋት ያለመ ሲሆን ይህ ግብ ከበለጸጉ ሀገራት ባገኘው "ጠንካራ ድጋፍ" ሊሳካ ነው። ነገር ግን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከእነዚያ ሀገራት የሚታየው የገንዘብ ድጋፍ ማሽቆልቆሉ - በተለይም የአሜሪካ መንግስት ሁሉንም የውጭ ዕርዳታዎችን ለማገድ መምረጡ ይህ ሙከራ እንዳያደናቅፈው ያሰጋል ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ በሽታን ለመዋጋት የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት የጋራ ፕሮግራም (UNAIDS) ሥራ 73 በመቶውን የሚሸፍነው ድጋፍ የምታደርግ መሆኑን የገለጹት ዊን ባይኒያማ ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ ገንዘቡን ባታነሳም ወደፊት ምን ዓይነት እርዳታ እንደሚደረግ ብዙ ግራ መጋባት አለ ብለዋል። የኤችአይቪ/ኤድስ በሽታን ለመዋጋት የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት የጋራ ፕሮግራም (UNAIDS) ዳይሬክተሯ "ሥርዓት ያለው" ወደ አሜሪካ አዲስ የውጭ ዕርዳታ ፖሊሲ መቀየር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡ “የሰዎች ሕይወት በየቀኑ በሚያገኙት መድኃኒት ላይ የተመካ ከሆነ ኳሱን መጣል ትክክል ሊሆን አይችልም" ብለዋል።

ወይዘሮ ዊን ቢያኒማ በኤድስ እና ኤችአይቪ ላይ በሚደረገው ትግል በእምነት ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች ሊጫወቱ የሚችሉትን ወሳኝ ሚና አጉልተው የተናገሩ ሲሆን በመጀመሪያ ፣ አሜሪካ ከበሽታው ጋር የምታደርገውን ትግል እንድትቀጥል እና የአውሮፓ ሀገራት የበለጠ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በማበረታታት “ዓለም አቀፋዊ አንድነትን” ማበረታታት ይችላሉ ብለዋል ።

የሃይማኖት ተቋማት በኤችአይቪ/ኤድስ የሚሰቃዩ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን መገለል መዋጋት እንደሚችሉም የተናገሩ ሲሆን ይህም ብዙዎች አሁንም ህክምና እያገኙ ያገደ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የኤችአይቪ/ኤድስ በሽታን ለመዋጋት የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት የጋራ ፕሮግራም (UNAIDS) ዳይሬክተር ወሮ ዊን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ቅድስት መንበር “የግብር ኢፍትሃዊነትን እንደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሥነ ምግባር ጉዳይ አድርገው በመቅረጻቸው” በማመስገን የተናገሩ ሲሆን ከዓለም አቀፍ ዕዳ መልሶ ማዋቀር ጋር - ኤች አይ ቪ እና ኤድስን ለመዋጋት የሚፈለጉትን ሀብቶችን ማሰባሰብ ይቻል ዘንድ የግብር ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

14 Feb 2025, 16:34