እ.አ.አ 2025 የዛይድ ሽልማቶች 'የእኛን የጋራ ሰብአዊነት' ያከብራሉ መባሉ ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እ.አ.አ የ2025 "ለሰብዓዊ ወንድማማችነት" የተሰኘው የዛይድ ሽልማት መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ለዓለም ሴንትራል ኩሽና፣ ለባርቤዶስ ሚያ ሞትሊ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የ15 አመቱ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ፈጣሪ ሄማን በቀለ ተሸልመዋል።
ሽልማቱ የተበረከተው ማክሰኞ ጥር 27/2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በአቡ ዳቢ መሀል ከተማ ነበር።
አሁን ስድስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የዛይድ ሽልማት በየዓመቱ በጥር 27 ቀን ይሰጣል። እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና አህመድ አል ታይብ ፣ የአል-አዝሃር ታላቅ ኢማም የተፈረመበት የሰብአዊ ወንድማማችነት የጋራ መግለጫ የታተመበት ቀን ነበር - የዛይድ ሽልማት መመስረትን ያነሳሳ ታላቅ ሰነድ መሆኑም ይታወሳል።
'የጋራ ሰብአዊነት'
በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ወደ መድረኩ የመጡት የመጀመሪያው አሸናፊ የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ነበሩ። እንደ ጠቅላይ ሚንስትርነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በወሰዱት ወሳኝ እርምጃ፣ እ.ኤ.አ. በ2030 ሀገሪቱን 100% የታዳሽ ሃይል ለመጠቀም ቃል መግባታቸው ይታወቃል።
የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ለተሰበሰቡት እንግዶች “ሰዎችን እና ፕላኔቷን መለየት አንችልም” ብለዋል ። የምንኖርበት ቦታ ከሌለ የሰው ልጅ እድገት ገቢራዊ ሊሆን አይቻልም። የዛይድ ሽልማት ትኩረት “በእኛ የጋራ ሰብአዊነት” ላይ የተመረኮዘ ነው ያሉ ሲሆን ትኩረት ሰጥተው “በእርግጥ አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች ላይ” ላይ ለማተኮር እድል መሆኑን ገልጸዋል።
በመቀጠል የአለም ሴንትራል ኩሽና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሪን ጎሬ ንግግር አድርገዋል። ድርጅቱ በሰብአዊ ቀውስ ለሚሰቃዩ ማህበረሰቦች የምግብ እርዳታ ይሰጣል። እ.ኤ.አ በጥቅምት 2023 ዓ.ም የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በጋዛ ላሉ ፍልስጤማውያን 100 ሚሊዮን የሚጠጋ እለታዊ ምግብ ሰጥቷል።
በመጨረሻም የ15 ዓመቱ የፈጠራ ባለሙያ ሄማን በቀለ ወደ መድረኩ ወጣ። በአሜሪካ በጆንስ ሆፕኪንስ ብሉምበርግ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት በሙከራ ላይ ያለውን ቀደምት ደረጃ የቆዳ ካንሰርን ለመከላከል እና ለማከም ወጪ ቆጣቢ ሳሙና ለመሥራት የራሱን ስልት ነድፏል፣ በዚህ የተነሳ ለሽልማት በቅቷል።
በሽልማቱ ወቅት በተሰጠው ገንዘን በትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የሆስፒታል ግንባታን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚያውለው ገልጿል።