ҽ

በሮም የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል በሮም የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰላም እና አንድነት እንዲሰፍን ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ በጂሜሊ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው ከሕመማቸው ማገገማቸውን በቀጥሉበት በአሁኑ ወቅት የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ከምያደርጉት አስተንትኖ በመቀጠል የምያስተላለፉትን ሳምንታዊ መልእክት ይፋ አድርጓዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው የኪነ ጥበብ ሥራ ሰዎችን አንድ ለማድረግ ያለውን ሚና በማጉላት በግጭት ቀጠናዎች ሰላም እንዲሰፍን ጸሎት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአካል በመገኘት ከምእመናን መካከል መሆን ባለመቻላቸው ማዘናቸውን የገለጹ ሲሆን  በጦርነት ለሚታመሰው የአለም ሀገራት ሰላም እንዲሰፍን ጸልየዋል፣ እናም በመተንፈሻ አካላት በሽታ ምክንያት በሮም ጂመሊ ሆስፒታል እየተደረገላቸው ላለው የህክምና አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሕክምና ባልደረቦቻቸው ሙሉ ዕረፍት ቢሰጧቸውም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥያቄ መሰረት የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት በኩል ባስተላለፉት የምስጋና እና የማበረታቻ መልእክት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ለባህል ዓለም አባላት በእነዚህ ቀናት ልዩ ኢዮቤልዩ ይከበራል በማለት ገልጸዋል።

የቅዱስነታቸው መልእክት በተለይ ለዚህ ልዩ ዝግጅት ለተሰበሰቡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በቫቲካን የተደረገውን መስዋዕተ ቅዳሴ አጉልቶ ያሳየ ሲሆን በሥነ ሥርዓቱም በቫቲካን የባሕልና የትምህርት ጉዳዮችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽኃፈት ቤት ዝግጅቱን እውን እንዲሆን ለማድረግ በመቻሉ ምስጋናቸውን ገልጸው ሥነ ጥበብን “ውበት የሚያሰራጭ እና ሰዎችን የሚያገናኝ ሁለንተናዊ ቋንቋ” ብለው ገልጸው መግባባትን የሚያበረታታ እና “የጦርነት ጩኸት ሁሉ” ጸጥ እንዲል ሊያደርግ የሚችል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ከእናንተ መካከል ብሆን እፈልግ ነበር፣ ነገር ግን እንደምታውቁት እኔ እዚህ ጂሜሊ ፖሊክሊኒክ ውስጥ ነኝ ምክንያቱም አሁንም ለብሮንካይተስ ሕመሜ የተወሰነ ሕክምና ስለምያስፈልገኝ ነው" በማለት ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ስለ ሰላም ጸሎቶች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ትኩረታቸውን ወደ ሞት፣ ውድመት እና መፈናቀል ወደ ዓለም አቀፍ ግጭቶች በማዞር በዩክሬን፣ በፍልስጥኤም፣ በእስራኤል፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በማያንማር፣ በኪቩ እና በሱዳን ጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ጸሎት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሕመማቸው ወቅት ለተደረገላቸው ድጋፍ አድናቆታቸውን ከመግለጽ ወደኋላ አላሉም፣ ምእመናንን ለጸሎታቸው እና ለጂሚሊ ሆስፒታል የሕክምና ባልደረቦች ላደረጉላቸው እንክብካቤ ምስጋና አቅርበዋል። "በዋጋ የማይተመን እና ኃላፊነት የተሞላው ሥራ ይሰራሉ ​​- በጸሎታችን እንርዳቸው" ብሏል።

የቅዱስነታቸው መልእክት የተጠናቀቀው “ጸጋ የተሞላችውን” የድንግል ማርያም አማላጅነቷን በመጠየቅ ሁሉም “አለምን የሚያድን የውበት ዘማሪና የሰላም የእጅ ጥበብ ባለሙያ” ይሆኑ ዘንድ ነው ምኞቴ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

17 Feb 2025, 15:42