ҽ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ አርቲስቶች የሰው ልጅ መንገዱን እንዳያጣ ይረዱታል ማለታቸው ተገለጸ።

በቫቲካን የባህልና የትምህርት ጉዳዮችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ጆዜ ቶሌንቲኖ የርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአርቲስቶች  እና የባህል ዓለም ኢዮቤልዩ ቅዳሴ ላይ ያደረጉትን ስብከት በንባብ አስተላልፈዋል። በውስጡም አርቲስቶች ውበትን በመፍጠር እውነትን እና መልካምነትን በመግለጥ ብቻ ሳይሆን በጊዜ እና በዓላማ ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተናግሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአርቲስቶች ኢዮቤልዩ እና በባህል ዘርፍ ለተሰማሩ ሰዎች በተዘጋጀው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ፈጣሪዎች "ኢየሱስ ባደርገው የአንቀጸ ብፁዓን ስብከት "እርሱም ወደ ደቀመዛሙርቱ ዐይኑን አነሣ፤ እንዲህም አለ፦ “እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና።” እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፤ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፤ ትስቃላችሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ፥ ሲለዩአችሁና ሲነቅፉአችሁ፥ በክፉም ስማችሁን ሲያጠፉ ብፁዓን ናችሁ! እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፤ በዚያን ቀን ተደሰቱ፤ በደስታም ዝለሉ፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና" (ሉቃስ 6፡20-24) የዚህ የኢየሱስ ስብከት አብዮታዊ ራዕይ ምስክሮች" እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአሁኑ ጊዜ በብሮንካይተስ ሕመም የተነሣ በሆስፒታል ውስጥ በሕክምና ላይ ሲሆኑ፣ የቫቲካን የባህልና የትምህርት ጽ/ቤት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሆሴ ቶለንቲኖ ደ ሜንዶንካ የቅዱስነታቸው ስብከት በንባብ መልክ አቅርበዋል።  

የዘላለም ደህንነት የምያስገኙ ኢየሱስ ስለ ብፅዕና የሰበከው ስብከት መመስከር ማለት ውበትን መፍጠር ብቻ ሳይሆን "እውነትን እና መልካምነትን መግለጥ… በታሪክ እቅፍ ውስጥ ተደብቆ" እና "ድምፅ ለሌላቸው ድምጽ መስጠት" ማለት ነው ብለዋል።

የህልውና ጥያቄዎችን ማንሳት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ስለ ሕይወት ጥልቅ ትርጉም ጥያቄዎችን የመጠየቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ያሳሰቡ ሲሆን ምንም እንኳን የምንኖረው "የገንዘብ እና ማህበራዊ ቀውሶች" ውስጥ ቢሆንም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ የእኛ "ከመንፈሳዊ ቀውስ ሁሉ በላይ የትርጉም ቀውስ" እየተስተዋል የገኛል ያሉ ሲሆን “ስለ ጊዜ እና ስለ ዓላማ ጥያቄዎችን እንድንጠይቅ እንዲረዱን አርቲስቶች ያስፈልጉናል፣ እኛ መንፈሳዊ ተጓዦች ነን? ወይስ ተቅበዝባዦች? ጉዟችን መድረሻ አለው ወይንስ አቅጣጫ የለሽ ነን? ብለን መጠየቅ ይገባናል ያሉ ሲሆን አርቲስቶቹ “የሰው ልጅ መንገዱን እንዳያጣ የመርዳት” ተግባር አለባቸው ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

ጥበብ እና ማስተዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ሌላው የኪነ-ጥበብ ቁልፍ ሚና ግለሰቦች መልካም እና ክፋን “ማስተጋባት” እንዲለዩ መርዳት ነው ያሉ ሲሆን አርቲስቶቹ ለእነዚህ ማስተጋቢያዎች “ትብ ወይም ቅርብ ናቸው” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ስለሆነም “እነሱን እንዲያብራሩልን እና በየትኛው መንገድ እንደሚመሩን እና እንዲያሳዩን ተጠርተዋል፡- ወይ አሳሳች የሳይሪን ዘፈኖች ወይም ለሰው ልጅ ትክክለኛ መንገዶችን ለማሳየት ተጠርተዋል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድ በመጥቀስ “በነፋስ የተበተነውን ገለባ” “በውሃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከሉ ዛፎች” ለመለየት በስራቸው ለሚሳተፉ ሰዎች መርዳት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሚና እንደሆነ ጠቁመዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ እለቱ ወንጌል እና የኢየሱስ ብፁዓን ስለተናግረው የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ሐሳባቸውን ያዞሩ ሲሆን በዚህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ውስጥ፣ “ኢየሱስ ድሆች፣ የተጨነቁ፣ የዋህ እና የሚሰደዱን እንደባረከ ያውጃል” - “የአስተሳሰብ ለውጥ” እና “የአመለካከት አብዮት” እዲመጣ ይፈልጋል ብለዋል።

አርቲስቶቹ በዚህ አብዮት ውስጥ እንዲሳተፉ ተጠርተዋል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስብከታቸው የገለጹ ሲሆን “መፈለግን፣ መጠይቅን እና አደጋን መጋፈጥን ፈጽሞ እንዳታቆሙ” በማለት አሳስበዋል።

 

17 Feb 2025, 15:44