ҽ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለካሪታስ፡- የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብርን ማስጠበቅ የእናንተ ዋነኛ ጥሪ ነው አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የካቶሊክ የዕርዳታ ድርጅት መሪዎችን በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ዕርዳታ ድርጅት የሰው ልጆችን ሰብዓዊ ክብር የማስጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ገልጸው፣ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት በሁሉም ቦታዎች እንዲጠበቅ ማድረግና ተጋላጭ የሆኑትን የመጠበቅ ግዴታ እንደሆነ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን አሜሪካ እና በካሪቢያን አካባቢ ከሚገኙት የካሪታስ ኢንተርንሽናሊስ የዕርዳታ ሰጪ ተቋም ፕሬዚዳንቶች እና ብሔራዊ ዳይሬክተሮች ጋር በሮም በተካሄደው የሥልጠና መርዓ ግብር ላይ በተገኙበት ነበር ይህንን መልእክት ያስተላለፉት። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የመንከባከብ ባህልን ለማዳበር የታለሙ ሂደቶችን በማጠናከር ላደረጉት ጥረት አመስግነዋል። "ሰብዓዊ መብትን መጠበቅ" ብለን እንጠራዋለን" ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ሰብዓዊ መብቶችን መጠበቅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስፓኒሽ ቋንቋ ባስተላለፉት መልእክት "መጠበቅ" የሚለው ቃል "ጥበቃ፣ መከላከል እና ዋስትና" ተብሎ ይገለጻል ያሉ ሲሆን ሆኖም፣ ከዚህ ትርጉም ጎን ለጎን ሌላም አለ፡- “በጦርነት ጊዜ ወታደሮቻቸው ጉዳት እንዳይደርስባቸው በከተማ መግቢያዎች ወይም በሮች ላይ በወታደራዊ አዛዦች ትዕዛዝ እንደሚሰጥ የሚያሳይ ምልክት ነው" ሲሉ አብራርተዋል።

ይህንን ሲገልጹ በመጀመሪያ ወደ አእምሮአቸው የመጣው ነገር ከነቢዩ ሕዝቅኤል እና ከመጽሐፈ ራእይ የተጻፈው ቃል ሲሆን ጌታም መልአኩን የጠየቀው “በሚተክዙና በሚያለቅሱ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክትን አድርግ" (ት. ሕዝ. 9፡4) በማለት ተናግሯል፣ የሚሠሩትን አጸያፊ ሥራዎችን እና ተግባሮችን ማጋለጥ ያስፈልጋል ብለዋል። 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተመለከቱት፣ በእውነቱ፣ ጌታ እኛን መልእክተኞቹን፣ “የእርሱን የተባረከ መስቀሉን ምልክት ወደ ዕርዳታ ድርጅታችን ካሪታስ በሚመጡት ሰዎች ሁሉ ግንባራቸው ላይ እናድርግ፣ እያዘኑና እየተከዙ፣ በተፈጸመባቸው ብዙ በደሎች፣ አስጸያፊ ድርጊቶችም ጭምር በሚሰቃዩ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት እናኑር" ብለዋል። 

በህይወታችን ሁሉ በሚያጋጥሙን እያንዳንዱ ሰው ላይ ይህን ምልክት “በእርግጥ” ማድረግ ማለት በክርስቶስ ወንድማማች ሆነው ክብራቸውን መቀበል ማለት እንደሆነ ገልጿል።

ኢየሱስ ለተግባራችሁ ይከፍላችኋል

ነገር ግን በመቀጠል “እንዲሁም ‘የተቀቡ ሕዝቦቼን አትንኩ’ የሚለውን የጌታን የማይቀር ግዴታ መቀበል ማለት ነው፣ ያሉት ቅዱስነታቸው ከዚህ አንጻር፣ መጠበቅ መለኮታዊ ስም ነው፣ ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “በወንድና በሴት ሁሉ ግንባር ላይ፣ በእያንዳንዳችን ልብ እንደ መስተዋት የታተመ ክርስቶስ ራሱ ነው” በማለት ያስረዳሉ። በትንንሽ የበጎ አድራጎት እና እንክብካቤ ተግባራት የፍቅሩ ተሸካሚዎች ለመሆን መመኘት ይኖርብናል ብለዋል።

በመጨረሻም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቦታው የተገኙትን ሰዎች ለምያደርጉት ጥረት እንዲክሳቸው፣ በሥራቸው መንፈስ ቅዱስ እንዲመራቸውና ቅድስት ድንግል ማርያም በመጎናጸፊያዋ እንድትሸፍናቸው ጸልየዋል፣ “ለሰዎች ሁሉ እንክብካቤንና ጥበቃን ማድረግ ከእሷ እንድትማሩ አደራ እላለሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

16 January 2025, 15:39