ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሱዳን እና በኮሎምቢያ ሰላም እንዲሰፍን ተማጽነዋል!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እ.ኤ.አ. በጥር 2023 ዓ.ም የጀመረው የሱዳን ግጭት እንዲቆም ቅዱስነታቸው እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም ካደረጉት የመላከ እግዚአብሔር ጸሎት በመቀጠል ባስተላለፉት በሳምንታዊው መልእክት የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በዓለም ላይ እጅግ የከፋውን ሰብዓዊ ቀውስ፣ በደቡብ ሱዳንም ቢሆን አሰቃቂ መዘዞችን እያስከተለ ነው” ሲሉ ጦርነቱ ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
በሱዳን ያሉ ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ እና በድርድር ጠረጴዛ ላይ እንዲቀመጡ ጋብዘው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰላም ድርድር እንዲደግፍ እና ሰብአዊ ርዳታ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።
"ከሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ጋር በቅርበት ቆሜ ወደ ወንድማማችነት፣ ወደ አንድነት፣ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶችን ለማስወገድ እና እራሳቸውን ልግጭት ማመመቻቸት የለባቸው ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም በኮሎምቢያ ካታቱምቦ ክልል ብዙ ሰላማዊ ሰዎች በተገደሉበት በታጠቁ ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት ከ 30,000 በላይ ሰዎች ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ያስገደዳቸው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። “ከእነርሱ ጋር ያለኝን ቅርርብ እገልጻለሁ እናም እጸልያለሁ” ብሏል።
የፀረ-ሴማዊነት አስፈሪነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል እሁድ የተከበረውን የዓለም የሥጋ ደዌ ቀንን አስታውሰዋል፣ ሁሉም ሰው የሃንሰን በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ከህብረተሰቡ ጋር እንዲያዋህዱ ለማድረግ እንዲሰሩ አበረታቷቸዋል።
የፊታችን ሰኞ ጥር 19/2017 ዓ.ም ከሚከበረው አለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን ቀደም ብሎ ጳጳሱ አውሽዊትዝ የማጎሪያ ካምፕ ነፃ ከወጣ ዘንድሮ 80 አመታትን አስቆጥሯል ብለዋል።
በሮም የምትኖረውን የሃንጋሪ ተወላጅ የሆነችውን ባለቅኔ ኢዲት ብሩክን ምሳሌ በማስታወስ “በእነዚያ ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዳውያንና የተለያየ እምነት ያላቸው ሌሎች ሰዎች ሲጠፉ የነበረው አስፈሪነት ፈጽሞ ሊረሳ ወይም ሊካድ አይገባም” ብሏል።
በተጨማሪም በናዚ የሞት ካምፖች ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖች የተገደሉ ሲሆን “ከመካከላቸውም ብዙ ሰማዕታት ነበሩ” ብሏል።
"ከየትኛውም ዓይነት አድልዎ እና ሀይማኖታዊ ስደት ጋር በመሆን የፀረ ሴማዊነት ቸነፈርን ለማስወገድ ሁሉም ሰው እንዲተባበር ጥሪዬን አድስሻለሁ"፥ "በአንድነት፣ ወጣቶች ለሁሉም ክፍት የሆነ ልብ እንዲኖራቸው በወንድማማችነት፣ በይቅርታ እና በሰላም መንፈስ በማስተማር የበለጠ ወንድማማች፣ ፍትሃዊ ዓለም እንገንባ" ብለዋል።
የኮሚዩኒኬሽን ኢዮቤልዩ
በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በኢዮቤልዩ ለዓለም የመገናኛ ብዙኃን ለመሳተፍ ወደ ሮም ለመጡት ሁሉንም የሚዲያ ባለሙያዎች ሰላምታ ሰጥተዋል። እናም ጋዜጠኞች “ሁልጊዜ የተስፋ ተራኪዎች እንዲሆኑ” አበረታቷቸዋል።