ҽ

የያንጎኑ አገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማውንግ ቦ የያንጎኑ አገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማውንግ ቦ  

ብፁዕ ካርዲናል ቦ በምያንማር በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደለው ካህን ጸለዩ፣ ዓመፅ እንዲቆም ተማጽነዋል!

የያንጎኑ አገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማውንግ ቦ በሚያንማር በታጣቂዎች በጭካኔ ለተገደሉት የመንዳላይ ሀገረ ስብከት ካህን የነበሩት አባ ዶናልድ ማርቲን ዬ ኒንግ ዊን ነፍስ ጸሎት ያደርጉ ሲሆን የሀገሪቱ ጳጳሳት መሪ ሁከቱ እንዲቆም እና ወደፊትም የዚህ ዓይነት ተግባራት እንዳይከሰቱ ሁሉም ጸሎት እንዲያደርግ ተመጽነዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ስፍር ቁጥር የሌላቸው ንፁሀን ዜጎች ደም እና መስዋዕትነት ከአባ ዶናልድ ማርቲን ዬ ኒንግ ዊን ጋር በመሆን በመላ ሀገሪቱ እየተከሰተ ያለውን ግፍ ለማስቆም እንደ መስዋዕትነት ያገልግሉ" ያሉት የማይናማር ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማውንግ ቦ በማይናማር ወታደራዊ እና ተቃዋሚ ሃይሎች መካከል ያለው ግጭት በቀጠለበት ወቅት በታጣቂ ቡድን ለተገደሉት አባ ዶናልድ ማርቲን ዬ ኒንግ ዊን ሞት ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ ግጭቱ እንዲያበቃ ሁሉም ምዕመናን መጸለይ ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገልጿል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የምያንማር ወታደራዊ መንግስት በበርማ ሰሜናዊ ምዕራብ ቺን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ሚንዳት በሚገኘው የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያንን በቦንብ ደበደበ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ. በጥር 25 ቀን የፈጠሩት አዲስ የተቋቋመው የሚንዳት ሀገረ ስብከት ካቴድራል ሆኖ የተመረጠችው ቤተ ክርስቲያን ነበረች።

'አመፅ እንዲቆም ልባዊ ጥሪ'

ብፁዕ ካርዲናል ቦ ለአባ ዶናልድ ባደረጉት የሐዘን መግለጫ ላይ፣ “የማንዳላይ ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ካህን ዶናልድ ማርቲን ኢ ኒንግ ዊን እ.አ.አ አርብ የካቲት 14 ቀን 2025 በታጣቂዎች በጭካኔ መገደላቸውን ዜና ደርሰናል።

በመላ ምያንማር የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ ከመንዳላይ ሊቀ ጳጳስ ማርኮ ቲን ዊን፣ ካህናቱ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንደሌይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምእመናን እና የበርማ ካህን ወላጆች እና ዘመዶች፣ በምያንማር የሚገኘው የቤተ ክርስቲያን ኃላፊ፣ ከእዚህ አለም በሞት እንዲለዩ በመደረጋቸው ሐዘናቸውን ገልጸዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ቦ “እግዚአብሔር አብ፣ የሕይወት ሁሉ ጌታ ከሐዘናችን ያጽናናን" በማለት ጸልየዋል።

"ከእነዚህ ካጋጠሙን አሳዛኝ ገጠመኞች በመማር የወንድማማችነት መንፈስ እንዲነቃቃ እና ጥቃቱ እንዲቆም አጥብቀን እንጠይቃለን" ሲሉ ተማጽኗል።

ለወደፊቱ እንደዚህ አይነት ክስተቶችን መከላከል

ብፁዕ ካርዲናል ቦ በአባ ዶናልድ ማርቲን ዬ ኒንግ ዊን ላይ የተፈጸመው በደል በቀላሉ የሚረሳ አይደለም ብለዋል።

"ስለዚህም ወደፊትም ይህን መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ይህንን ጉዳይ የፈጸሙ ሰዎች ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ እና ፍትህ እንዲሰፍን እናሳስባለን" ብለዋል።

"የአባ ዶናልድ ማርቲን ዬ ኒንግ ነፍስ በእግዚአብሔር ምሕረት ትረፍ" ሲሉ የሐዘን መግለጫቸውን ደምድሟል፣ "ነብሳቸው በዘላለም ሰላም ትረፍ!" አክለው ገልጸዋል።

 

17 Feb 2025, 15:49