ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልእክት ምስጋናቸውን መግለጻቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"የሰውን ሁሉ ክብር የጠበቀ ማህበረሰቦቻችንን ለመገንባት ሰብዓዊ የሆነ ስርዓቱን የጠበቀ የስደተኞች ሕግ እንዲኖር እንደ ሀገር ድፍረት እንድናገኝ ቀጣይ ፀሎታችሁን እጠይቃለሁ" ብለዋል።
የአሜሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ (USCCB) ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለአሜሪካ ጳጳሳት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላኩት ስደተኞችን የተመለከተ መልእክት የምስጋና ደብዳቤ ላይ ይህንኑ ገልጸዋል።
ለሁሉም ተስፋ የሚሰጥ መልእክት ነው
“የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደመሆኖ መጠን፣ እያንዳንዱን ካቶሊክ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን ክርስቲያን በእምነት አንድ የሚያደርገንን ነገር እንድታከናውኑ ተጠርታችኋል —ለእያንዳንዱ ሰው፣ ዜጋ እና መጤ የኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ አቅርቡ” ሲሉ አመስግኗል።
የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዘዳንት "በእነዚህ የፍርሀት እና የግራ መጋባት ጊዜዎች፣ ለአዳኛችን 'ለእነዚህ ከታናናሾቻችን ለአንዱ ምን አደረክ?' የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ መሆን አለብን" ብለዋል።
ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን መርዳት
ከዚህም በላይ ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ "ድንገተኛ ዕርዳታ በመቋረጡ የሚሰቃዩ ቤተሰቦች ለመጽናት የሚያስችል ጥንካሬ እንዲያገኙ" ወደ ጌታ እንዲጸልዩ ምእመናን ሁሉ እንዲተባበሩ የጋበዙ ሲሆን የአሜሪካው ሊቀ ጳጳስ፣ “ከአንተ ጋር፣ የአሜሪካ መንግሥት ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን ለመርዳት የገባውን ቃል እንዲጠብቅ እንጸልያለን" ብለዋል።
የአሜሪካ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት በደብዳቤያቸው ላይ የካቶሊክ የእርዳታ አገልግሎቶችን ብሔራዊ ስብስብ ይህንን በሚቀጥለው ጊዜያት የምጀመረውን የዐርባ ጾም ወቅት ምጽዋት በመስጠት በመደገፍ እንዲሁም በአካባቢው የካቶሊክ በጎ አድራጎት ድርጅቶች “ክፍተቱን በሁሉም ጥረት እንዲሞላ” ከእግዚአብሔር ሕዝብ ምሕረትና ልግስና ጠይቀዋል።
"በመካከላችን ለችግረኞች የምናደርገውን እንክብካቤ ለመቀጠል ስንታገል እና ስደተኞች ወደ ባህር ዳርቻችን በሚመጡባቸው ቦታዎች ያለውን ሁኔታ ለማሻሻል ፍላጎታችን ነው" ሲል አጉልቶ ተናግሯል "በእነርሱ ውስጥ የክርስቶስን ፊት እንደምናይ ሁልጊዜ እናስታውሳለን" ብለዋል።
በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ "የእርቅ፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት ድልድይ እንገንባ" በማለት ከገለጹ በኋላ ምልእክታቸውን አጠናቀዋል።