ҽ

In Lombardia il maltempo 'annulla' befane e cortei dei magi

ሰብአ ሰገል ከምስራቅ የመጡ የከዋክብት ተመራማሪዎች ጠቢባን ናቸው፡፡

ሰብአ ሰገል ከምስራቅ የመጡ የከዋክብት ተመራማሪዎች ጠቢባን ናቸው፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት ብዙ ዘመናት ነቢዩ ኢሳይያስ ክርስቶስ ከተወለደ አይሁዳውያን ብቻ ሳይሆኑ አረማውያንም ጭምር እንደሚሰግዱለት በትንቢት ቃሉ አብራርቶ ተናግሮ ነበር፡፡ “ኢየሩሳሌም ሆይ ተነሺ መብራትሽን አብሪ ብርሃንሽ መጥቶአልና፡፡

የእዚህ ዝግጅት አቅታቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የእግዜአብሔር ክብር በአንቺ ላይ በራ፡፡ ሕዝቦችና ነገሥታት በብርሃንሽ ይራመዳሉ፤ ከሳባ ወርቅና ከርቤ ይዘው ሊመጡ ነው፤ የእግዚብሔርን ደኀንነት ሊናገሩ ነው እያለ እየሩሳሌምን በተስፋ መድኃኒት ያጽናናት ነበረ (ኢሳያስ 60፡1)። ኢየሱስ ተወልዶ እንደ ሙሴ ሕግ ወደ ቤተመቅደስ እንዲቀርብ በሄደ ጊዜ ቅዱስ ስምኦን ይህ ሕፃን ለዓለም ሕዝቦች ብርሃን እንደሚሆን አስቀድሞ በትንቢት ተናገረ (ሉቃስ 2፡32) መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ መጀመሪያ እረኞች ቀጥሎም ሰብአ ሰገል የተባሉ የክዋክብት ተመራማሪዎች ጠቢባንና አዋቂ ሰዎች የዓለምን ንጉሥ እጅ እንዲነሱ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መጡ፡፡

በእረኞች በመልአክ ቃል ሰብአ ሰገል ግን በተአምራዊው ኮከብ ተጠርተውና ተመርተው መጡ፡፡ እነርሱ እግዚአብሔር ከጠራቸው በኋላ የመንገዳቸውን ችግር ሳያስቡ ቤተሰቦቻቸውን፣ አገራቸውንና ጉዳያቸውን ትተው ትልቅነታቸውን ረስተው የአምላክን ልጅ ለማክበር ይሉኝታ ሳይፈሩ በፍጥነት ከአገራቸው ተነስተው ወደ ሩቅ አገር ሄዱ፡፡ ሰብአ ሰገል ራስህንና ጉዳይህን ትተህ እንዴት አድርገህ አምላክን እንደምታስብና እንደምታገለግል እርሱ ሲጠራህ በጥፍነት መልስ መስጠት እንሚያስፈልግ ያስተምሩናል፡፡ እግዚአብሔርን የሚወዱ የማያደርጉትና የማይደርሱበት የላቸውም፡፡ እርሱን ለማስደሰት ሲሆን ችግር ምን መሆኑን አያውቁም፡፡

አግዚአብሔር በብዙ መንገድ ቃሉን ሲያሰማን በሹክሹክታ ሲነግረንና ሲገልጥልን ፈቃዱን ሲያስታውቀን እንዴት አድርገን ተቀብለን እንመለስለታለን; እንደ ሰብአ ሰገል በደስታና በፍጥነት ወይስ በሃኬትና በመዘንጋት ወይም የባሰ አውቀን ዝም እንላለን; እዚህ ላይ ተመልሰን ያለፈ ሕይወታችንን እንመርምርና ተገቢውን መልስ እንስጥበት፡፡ የከዋክብት ተራማሪዎች ወደ ኢየሩሳሌም እንደገቡ ወደያው “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት አለ; በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጣን” እያሉ ስለ ኢየሱስ ጠየቁ፡፡ በሁሉ ዘንድ ፈለጉት የእግዚአብሔርን ፍላጐትና ምኞት ያላቸው ስለሆኑ ሁሉን ነገር ረስተው በልባቸው ይፈልጉታል፣ ሳያገኙተም አያርፉም፡፡ እኛስ እንደዚህ ያለ የአምላክ ምኞት አለን ወይ; እስቲ ረጋ ብለን እናስተውል ልባችንን ጠንቀቅ ብለን እንመርመር፡፡

ሰብአ ሰገል በግንበራቸው ተደፍተው ሰገዱለት፡፡ ያመጡትንም እጅ መንሻ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ አቀረቡለት፡፡ እኛስ ኢየሱስን ሰናገኝ እንደዚህ እንደሰታለን ወይስ እንደ ድሮአችን ቀዝቃዛዎች ሆነን እንቀራለን; በቅዱስ ቁርባን ስንቀበለው ስንት ጊዜ በቀዝቃዛነትና በቸልተኛነት እንቀበለዋለን; ይህን የሚያሳዝን መንፈስ ጐዶሎነት ይዘን እንጠብቀዋለን፡፡ እንዴት ያለ የሰብአ ሰገል መንፈሳዊነትን እንልበስ፤ አንደ እነርሱ የሚቃጠል የአምላክን ፍቅር በልባችን ውስጥ እናሳድር በፍቅሩ ተስበን በሁሉም ስፍራ በታላቅ ምኞች እንፈልገው፡፡

11 January 2025, 10:51